Abba Gorgoryos Biosphere Coffee

Ludolfs Laufbahn im Dienst Herzog Ernsts des Frommen von Sachsen-Gotha lud 1652 den äthiopischen Gelehrten Abba Gorgoryos nach Gotha ein, wo beide mit der Erarbeitung eines Lexikons den Grundstein der Äthiopischstudien legten. 

 

This product is made in memory of Abba Gorgoryos arrival to Gotha in the year 1652. Along with Hiob Ludolph he establishes the Gotha Religious Colloquies, they go through the library’s old writings and together they compile a dictionary.

 

በቅርብ ቀን ከውጤቶቿ አንዱ የሆነውን ያገራችንን ቡና ምስል እታች እንደሚታየው አድርጋ ላከችልኝ። ልቤን በጣም በስሜት ነካው። መረኳት! አወደስኳት! ምክንያቱም ቡናውን የሰየመችው ባልተዘመረላቸው ያገራችን ድንቅ ምሁር በአባ ጎርጎሪዎስ ስም ስለሆነ ነው የኔ የምርቃት ብዛት።

አባጎርጎሪዎስ 1587 መካነ ኢየሱስ የተወለዱና በዚያን ዘመን ባገራችን የነበረውን ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያን ትምሕርትና በሚደንቅ ሁኔታ ቲሪካችንን በጥልቅ የሚያውቁ ምሁር ነበሩ። የቃላትና የሰዋስው የአማርኛም የግእዝንም ምስጢር ሙሉ ለሙሉ በአእምሮዋቸው ሰሌዳ መዝግበው የሚንቀሳቀሱ ቤተ መጻሕፍት ነበሩ ብል ማጋነን አይሆንም። አባ ጎርጎሪዎስን ታወቂ ያደረጋቸው በዚያን ዘመን በብዙ ችግርና መከራ ተጉዘው በጀርመን አገር የነበራቸው ቆይታ ነበር። እዚያም በነበሩበት ዘመን ሒዩብ ሉዶል ከሚባል የጀርመን ምሁር ጋር በመተባበር ስለ ኢትዮጵያ ኢንሳይክሎፒዲያ (እንደኔ ግምት ካልተሳሳትኩ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም) የአማርኛና የግእዝ መዝገበ ቃላት ከላቲን ትርጉም ጋር የኢትዮጵያ ታሪክ ባሕልና ጂዎግራፊ የመሳሰሉትን በጽሁፍ እንዲወጣ ያደረጉ ምርጥና እጹብ ያገራችን ድንቅ ምሁር ነበሩ። በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያ ስነ መለኮትና የቤተ ክርስቲያን ታሪክና ስርአት እንዲጻፍ ተባብረዋል። አባ ጎርጎሪዎስ እዚያ ያገኙትን እውቀት ላገራቸው ልጆች ለማስተማር በመርከብ ሲመጡ 1658 በመርከቧ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው ጠፍቷል። ምነው በመጡልን ነበር። ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኔራለች Abebe Haregewoin

8,33 €

  • 0,25 kg
  • verfügbar
  • 1 - 3 Tage Lieferzeit1